Online Admission ኮሌጁ የተሟላ አገልግሎትን ያካተተ ስልጠና የሰጠበትን ቆይታ በስኬት አጠናቀቀ

ኮሌጁ የተሟላ አገልግሎትን ያካተተ ስልጠና የሰጠበትን ቆይታ በስኬት አጠናቀቀ

15th July, 2026

እሁድ:- ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
 
ኮሌጁ የተሟላ አገልግሎትን ያካተተ ስልጠና የሰጠበትን ቆይታ በስኬት አጠናቀቀ!!
 
አንጋፋው ጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከቦንጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለመጡ አሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረውን የ10 ቀናት የተጠናከረ የአሉሚኒየም ስራዎች አፕሊኬሽን (Aluminum Works Applications Skill Training) ክህሎት ስልጠና በስኬት በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት አበረከተ።
 
በኮሌጁ የማታ ተከታታይ ትምህርት እና የአጫጭር ስልጠና ማስተባበሪያ እንዲሁም በሜታል ማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት ትብብር የተዘጋጀው ይህ ስልጠና ከሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ10 ተከታታይ ቀናት ተሰጥቷል።
 
ስልጠናው የቦንጋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች (Trainers) በዘርፉ ያላቸውን የተግባር ክህሎትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሳደግ በተቋማቸው የላቀ የስልጠና ጥራት እንዲያረጋገጡ ያለመ ነው።

በስልጠናው ማጠቃለያ መርሃ ግብርም ክህሎታቸውን ላዳበሩ 9 አሰልጣኞች የስልጠና ተሳትፎ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with