ማክሰኞ፡- ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በማኔጅመንት እና በአካዳሚክ ኮሚሽን ደረጃ ዛሬ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ግምገማ ተካሄደ፡፡
ሁሉም የኮሌጁ ማናጅመንት እና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት በተገኙበት የበጀት ዓመቱ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በቀረበው ሪፖርት መረጃ መሰረት በበጀት ዓመቱ የሰልጣኞች ቅበላና የስልጠና ሂደት፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ትግበራና የቴክኖሎጂ ልማት ሂደት፣ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር፣ የተቋሙን መሰረተ ልማት ከማስተካከል አኳያ፣ ተቋማዊ ሪፎርም ከመተግበር ረገድ እና ሁሉም አካል በየዘርፉ ተነሳሽነት እና ቅንጅት ፈጥሮ ስራዎችን ከመከወን አንፃር እምርታዊ ለውጥ ያሳየ እና ስኬታማ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በቀጣይ ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ መሟላት ያለባቸው ግብዓቶችና መተግበር የሚኖርባቸው አሰራሮች እንዲሁም ከአካባቢ የመልማት ፀጋና ተከታታይ የሪፎርም ትግበራ ጋር ተያይዞ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም የ2018 በጀት ዓመት ዝግጅት ምዕራፍ ላይ በርብርብ የሚተገበሩ ዋና ዋና ተግባራት ተገልጸውና ውይይት ተደርጎባቸው የዕለት መድረክ ተጠናቋል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
መረጃዎችን በአማራጭ ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉ