ማክሰኞ:- ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
የመለኪያ መሳሪያዎች ፍተሸ ተካሄደ!!
በኮሌጁ ማሰልጠኛ ወርክ ሾፖች የሚገኙ የመለኪያ መሳሪያዎች ፍተሻ ተከናወነ፡፡
ኮሌጁ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ስነ ልክ ኢንስቲትዩት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ከ7 ዲፓርትመንቶች ለተውጣጡ 95 የስልጠና መሳሪያዎች የጥራት ደረጃቸውን ለማስለካት ታቅዶ 77 ለሚሆኑት የማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በተደረገው የጥራት ፍተሻም የሚሰሩ፣ የማይሰሩ፣ የሚስተካከሉ እና የሚወገዱ የሚል ደረጃም ተቀምጦላቸዋል፡፡
ኮሌጁ በአይሶ 9001፡2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት የተመዘገበ በመሆኑ ስታንዳርድዱን አስቀጥሎ ለመሄድ ያግዘዋል ተብሏል።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››